Entries by tc

ካህናት

አባ ገብረጊዮርጊስ ካሳዬ :- አስተዳዳሪ ቀሲስ ዶ/ር ኃይለኢየሱስ አለባቸው ቀሲስ ስመኘው ጌትዬ:- ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዲ.ን ተሻለ ቢያዝን ዲ.ን ሳምሶን ዲ.ን ተስፋልደት ዲ.ን አብርሃም

ቃለ አዋዲ እና መተዳደሪያ ደንብ

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የመተዳደርያ ደንብ ረቂቅ ከግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗን የአገልግሎት አድማስ ማስፋት እና ማስቀጠል እንዲቻል ዋናው ቃለ ዓዋዲ በሚገባ ተጠብቆ፤ ይህ አጥቢያው የሚመራበት የመተዳደሪያ ደንብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ሳይወጣ አጥቢያው የተመሠረተበትን ሀገር አሠራር እና ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ […]

የአጥቢያው የመተዳደርያ ደንብ ጸድቆ በሥራ ላይ ዋለ

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የመተዳደርያ ደንብ ረቂቅ በሀ/ስብከቱ ታይቶ እና ታርሞ በሥራ ላይ እንዲውል ተፈቀደ። የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኗን የአገልግሎት አድማስ ማስፋት እና ማስቀጠል እንዲቻል ዋናው ቃለ ዓዋዲ በሚገባ ተጠብቆ፤ ይህ አጥቢያው የሚመራበት የመተዳደሪያ ደንብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ሳይወጣ አጥቢያው የተመሠረተበትን ሀገር አሠራር እና ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ […]

ቀዳሚት ሥዑር

  ቀዳሚት ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አርፎ የዋለባት ዕለት በመኾኗ ‹ቀዳሚት ሥዑር› ወይም ‹ቀዳም ሥዑር› ትሰኛለች፡፡ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እኽል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው […]

ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት

  በዓቢይ ጾም ከሰርከ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፤ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፤ አክፍሎት፤ ቄጤማ ማሰር፤ ጥብጣብ፤ ጉልባን እና ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለ እነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈጻጸም መዛግብት […]

ሆሣዕና

በመ/ር ኃይለ ማርያም ላቀው መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የኾነው ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደ ተቀመጠ ዅሉ ዛሬም ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት አድሮ የሕሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፡፡ እርሱ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅምና (መዝ. ፶፥፲፯፤ ኢሳ. ፷፮፥፪)፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች […]

የኪዳነምሕረት በዓል አከበሩ

በመ/ጸ/ቅ/ስ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤት ታዳጊዎች አመታዊ የኪዳነምሕረት በዓል አከበሩ የካቲት 11 ቀን 2009 ዓም የኪዳነምሕረት ማህበር አባላት ወይንም የቤተ ክርስትያኑ ሰንበት ት/ቤት ታዳጊዎች በደመቀ ሁኔታ አመታዊ የኪዳነምሕረትን በዓል አክብረዋል። የአገሪቱ ሁኔታ የኪዳነምሕረትን በዓል በቀኑ ለማክበር አስቸጋሪ ቢያደርገውም የማህበሩ አባላት ቀደም አድርገው ቅዳሜ ቀን የካቲት 10 ላይ በሰፊው አክብረዋል። በአሉንም በደብሩ አስተዳዳሪ በአባ ገብረ ጊዮርጊስ ጸሎትና ቡራኬ የተጀመረ ሲሆን፤ […]

+++ የበገና እና የሥነ ጽሑፍ ምሽት +++

============================ ቅዳሜ ሚያዚያ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ከ14:00 ሰዓት ጀምሮ(Lör. Apr. 23, 2016) Kl. 14:00ቦታ:- Nacka/Centralplan, Värmdövägen 622, 132 41 Saltsjö-booBuss: 422, 444, 471, från Slussen============================በመርሐ ግብሩ:- ወቅቱን ያገናዘቡ የበገና መዝሙራት፥ ሥነ ግጥም፥ ስብከተ ወንጌል፥ መዝሙር በሕጻናት እና በሰ/ትቤቱ መዘምራን ይቀርባሉ።በሰዓቱ በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ።============================አዘጋጅ:- በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ምዕ/አውሮፓ አህጉረ ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት {flike}{plusone}