Entries by tc

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

ማሳሰቢያ:- +++ የዕለተ ዓርብ የጉባኤ ቦታ ወደ St. Jacobs Kyrka ተቀይሯል። (Västra Trädgårdsgatan 2, T-bana: Kungsträdgården, ከኋላ ይውረዱ) ሙሉ መረጃውን ከታች ይመልከቱ። እግዚአብሔር አምላክ ጉባኤያችንን ያቅናልን። +++ “የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” ራእይ 22፥17 {flike}{plusone}

አንግሰነው መጣን ቅዱስ ዑራኤልን

በጽዮን ጌታቸው ነሐሴ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. አንግሰነው መጣን ቅዱስ ዑራኤልን የተቦሪ ካሉት ወገኖች ጋር አብረን መንፈስን የሚያድስ ጊዜን አሳልፈን በደስታ በፍቅር በአንድነት ሆነን።    ተሰባሰብንና አርብ ከሰአት    እመሃል ከተማ ተቃጠርንበት። በጸሎት ጀመርነው መንገዳችንን አምላክ በቸርነት በሰላም አድርሶ እንዲመልሰን።    ፍቅራችን ሲያስደስት እንዲሁ’ ዝማሬያችን    ስናደርስ ምስጋና ለቸሩ አምላካችን። በመሃሉም አረፍ አልንና ለምሳ ከወደ አገልግሉ […]

አንግሰነው መጣን

 ከፅዮን ጌታቸው አንግሰነው መጣን ቅዱስ ኡራዔልን የተቦሪ ካሉት ወገኖች ጋር አብረን መንፈስን የሚያድስ ጊዜን አሳልፈን በደስታ በፍቅር በአንድነት ሆነን    ተሰባሰብንና አርብ ከሰአት    እመሃል ከተማ ተቃጠርንበት በጸሎት ጀመርነው መንገዳችንን አምላክ በቸርነት በሰላም አድርሶ እንዲመልሰን    ፍቅራችን ሲያስደስት እንዲሁ’ ዝማሬያችን    ስናደርስ ምስጋና ለቸሩ አምላካችን በመሃሉም አረፍ አልንና ለምሳ ከወደ አገልግሉ ምግብ ልናነሳ

ጉባያችን እንዲህ አለፈ

አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተዉ ምግብ ተመግበው እንዲሁም የይስሃቅን መወለድ አብስረዉ የወጡበትን ዕለት የምንዘክርበት ለኛም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ስቶክሆልም ጉባዔ አስተባባሪ ኮሚቴ በጉጉት እና በደማቅ ዝግጅት ስንጠብቀው የነበረዉ ቀን ደርሶ እንዲህ በደማቅ እና ፍቅር በተሞላበት አገልግሎት አክብረነው አለፈ። እሁድ ሐምሌ 6 ጠዋት በደብሩ እና በእንግዶች ካህናትና ዲያቆናት በተአምረ ማርያም : በኪዳነ […]

በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ

በአባ ገ/ጊዮርጊስ ካሳዬ ግንቦት 21፣ 2006 ዓ.ም. ዕርገት የሚለው ቃል መገኛው የግእዝ ቋንቋ ሲሆን፡- መገኛ ቃሉም “ዐረገ” = “ከፍ አለ፣ ወጣ” የሚለው የግዕዝ ግሥ ይሆናል። ዕርገት ማለት ደግሞ = ከፍ ማለት፣ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው። በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ዕርገት ሁለት ዓይነት ነው፡- v የኅሊና ዕርገት እና v የአካል ዕርገት

በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ

በአባ ገ/ጊዮርጊስ ካሳዬ ግንቦት 21፣ 2006 ዓ.ም. ዕርገት የሚለው ቃል መገኛው የግእዝ ቋንቋ ሲሆን፡- መገኛ ቃሉም “ዐረገ” = “ከፍ አለ፣ ወጣ” የሚለው የግዕዝ ግሥ ይሆናል። ዕርገት ማለት ደግሞ = ከፍ ማለት፣ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው። በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ዕርገት ሁለት ዓይነት ነው፡- v የኅሊና ዕርገት እና v የአካል ዕርገት

የትንሣኤ 2 መዝሙርና ምንባባት

የትንሣኤ 2 መዝሙር (ከመጽሐፈ ዚቅ) ትትፌሣሕ ሰማይ ወትታኃሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይጸውዑ አድባር ወአውግር ወኩሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ፡፡ ትርጉም: ሰማይ ይደሰታል ምድርም ትደሰታለች የምድር መሠረቶችም ቀንደ መለከትን ይንፉ /ይደሰቱ/ ተራሮችና ኮረብቶችም /ነገሥታት መኳንንት/ ይጩኹ/ይደሰቱ/ የምድረ በዳ እንጨቶችም ይጩኹ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ ምድርም […]

የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን –በዓብይ ኋይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን – አግዐዞ ለዓዳም ሰላም  –እም ይእዜሰ ኮነ –ፍስሃ ወሰላም «ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም፣ ወከመ ኀያል ወኅዳገ ወይን፣ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ = እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው ኀያል ሰውም፣ ጠላቱን በኋላው ገደለ፡፡»       የሚቀጥለው ሊንክ በመጫን ተጨማሪ ፎቶዎችን ይመልከቱ – የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም  

ጸሎተ ሐሙስና ዓርብ ስቅለት በፎቶ ሲቃኝ

“ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ። እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው። ጴጥሮስም። የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም። ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት። ስምዖን ጴጥሮስም። ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው። ኢየሱስም። የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ […]

የትንሣኤው ትርጉም በዓሉና አከባበሩ

ከሊቀ ትጉሃን ኀ/ጊዮርጊስ ዳኘ በጠ/ቤተ ክህነት የዕቅድና ልማት መምሪያ ምክ/ሓላፊ «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡  መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡ «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡  «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡ «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = […]