Entries by tc

ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ

መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት በስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሌላቸው ሥልጣን አሽገው የምእመናንን የአምልኮ ነጻነት ለመገደብ በሞከሩ እና ችግሩ በሰላማዊ እና በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ ሀገረ ስብከቱ ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥረቶች ካለመቀበል አልፈው ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተላለፈው […]

መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)

  የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) አምላኩሰ ለአዳም ለዕረፍት ሰንበተ ሠርዓ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ ወይቤሎሙ ኢየሱስ አነኒ እገብር አንትሙኒ እመኑ ለግብርየ ወይቤሎሙ አነ ውእቱ እግዚኦ ለሰንበት እግዚኦ ውእቱ ለሰንበት ወልድ ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውህ ሊተ እኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር እስበክ ግዕዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ ትርጉም: “የአዳም ፈጣሪ ለዕረፍት ሰንበትን ሠራ፤ አይሁድም […]

አውደ ወራዙት (ወጣትነት በቤተክርስቲያን)

“ልጆቻችሁ በጐልማሳነታቸው እንደአትክልት አደጉ ፡፡ ሴቶች ልጆቻችሁም በግንብ ሥር እንዳለ አንደተወቀረ የማዕዘን ዐምድ ይሆኑ ዘንድ” መዝ.4 ፡ 02 ወጣትነት ምንድን ነው ወጣትነት የሚለው ቃል ታላቅና ለጆሮ የሚያስደስት ቃል ነው፡፡ ወጣትነት በሰው ልጅ እድሜ ቀመር የእሳትነት ወቅት የሚባልው ሲሆን በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከ15 እስከ 50 ወይም ከ20 እስከ 40 ዓመት ያለውን እድሜ ክልል ያጠቃልላል፡፡ በኢትጵያ ህግ መሠረት […]

ጾምና ጥቅሙ

ከሊቀ ጉባዔ ቀለመወርቅ ውብነህጾም ለተወሰነ ሰዓት ከሁሉም ምግብ መከልከል፣ ሁሉንም ምግብ መተው ሲሆን ለተወሰነ ቀናት ማለት የጾሙ ቀናት እስኪያልፍ ድረስ ከተወሰኑ ምግቦች መከልከል የተወሰኑ ምግቦችን መተው ነው፡፡ ይህም ጥሉላትን ፈጽሞ መተው፣ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጾም ከጥሉላት ምግቦች መከልከል ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጆችን ከሚጎዳ ነገር ሁሉ መከልከልና ለሌሎች መልካም ሥራ መሥራትንም ይጨምራል፡፡ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ […]

አገልግሎት

1. የቅዳሴ/የማኅሌት/የሰዓታት/የነግህ ጸሎት /የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መደበኛ የቅዳሴ  አገልግሎት በየሳምንቱ እሑድ (Every Week Sunday Morning) ከጥዋቱ 1 ሰዓት (7:00 AM) ጀምሮ በየወሩ በ7 – የሥላሴ ዕለት እና በ 14 – የአቡነ አረጋዊ ዕለት በዓመት በዓላት ዕለት (ለምሳሌ የዓመቱ የመላእኩ ቅዱስ ገብርኤል በዓል፣ እርገት ወዘተ) 2. የሠርክ ጸሎትና ስብከተ ወንጌል     ዘወትር ረቡዕ ና ዓርብ ከምሽቱ […]

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ምርጫ አካሄደ

ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ እና ሥራ አስኪያጁ መጋቤ አእላፍ ተወልደ ገብሩ እንዲሁም የአጥቢያው ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በተገኙበት የካቲት 02 ቀን 2006 ዓ.ም. በ S:t Jacobs Kyrka, […]

ታሪክ

የመ/ጸ/ቅ/ሥ/ ቤተክርስቲያን አጭር የምስረታና የአገልግሎት ዘመን ትውስታ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ታቦተ ሕግ ቅድስት ሀገር ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገረ ስብከት ገዳም በልዑል እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልንና በቆሞስ አባ ወልደ መስቀል ደምሴ አማካኝነት ጥር 12 ቀን 1998 ዓ.ም. ወደ ሀገረ ስዊድን ስቶክሆልም ከተማ በክብር ደረሰ። ይህንንም ተከትሎ እ.ኤ.አ. ጥር 21 ቀን […]

ለየካቲት 23 2006 ዓ.ም. (March 2, 2014) በ Vårby skolan ይካሄዳል ተብሎ የተጠራውን ስብሰባ ሀ/ስብከቱ እውቅና የማይሰጠው መሆኑን ገለጸ

እንደሚታወቀው በምእመናን እና በቤተ ክርስቲያኑ የቀድሞ የሰበካ አስተዳደር መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና በአስተዳደሩ በተወሰደው ቤተ ክርስቲያንን የማሸግ ኢ-ቀኖናዊ እርምጃ ላይ መፍትሄ ለመስጠት የሰ/ም/አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ከአንድም ሁለት ጊዜ ወደ ስቶክሆልም መምጣታቸው ይታወሳል። በእነዚህ ሁለት አበይት ስብሰባዎች የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ልዑካን እና ምእመናን በተገኙበት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ሃሳባቸውን እንዲያስረዱ […]