ቀዳሚት ሥዑር

 

ቀዳሚት ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አርፎ የዋለባት ዕለት በመኾኗ ‹ቀዳሚት ሥዑር› ወይም ‹ቀዳም ሥዑር› ትሰኛለች፡፡ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እኽል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 {flike}{plusone} 

ሆሣዕና

በመ/ር ኃይለ ማርያም ላቀው

መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የኾነው ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደ ተቀመጠ ዅሉ ዛሬም ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት አድሮ የሕሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፡፡ እርሱ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅምና (መዝ. ፶፥፲፯፤ ኢሳ. ፷፮፥፪)፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜአችን ሳትጠልቅ በእምነት እግዚአብሔርን እንፈልገው፡፡ ሰላሙን ይሰጠን ዘንድም ንስሐ ገብተን ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› እያልን እናመስግነው፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

{flike}{plusone} 

ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት

መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.

በዓቢይ ጾም ከሰርከ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፤ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፤ አክፍሎት፤ ቄጤማ ማሰር፤ ጥብጣብ፤ ጉልባን እና ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለ እነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈጻጸም መዛግብት አገላብጠን፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን አነጋግረን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

አንግሰነው መጣን

 ከፅዮን ጌታቸው

አንግሰነው መጣን ቅዱስ ኡራዔልን

የተቦሪ ካሉት ወገኖች ጋር አብረን

መንፈስን የሚያድስ ጊዜን አሳልፈን

በደስታ በፍቅር በአንድነት ሆነን

   ተሰባሰብንና አርብ ከሰአት

   እመሃል ከተማ ተቃጠርንበት

በጸሎት ጀመርነው መንገዳችንን

አምላክ በቸርነት በሰላም አድርሶ እንዲመልሰን

   ፍቅራችን ሲያስደስት እንዲሁ ዝማሬያችን

   ስናደርስ ምስጋና ለቸሩ አምላካችን

በመሃሉም አረፍ አልንና ለምሳ

ከወደ አገልግሉ ምግብ ልናነሳ Read more

ጉባያችን እንዲህ አለፈ

ቅድስት ሥላሴ በዓለ ንግስ በከፊል - ስቶክሆልምአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተዉ ምግብ ተመግበው እንዲሁም የይስሃቅን መወለድ አብስረዉ የወጡበትን ዕለት የምንዘክርበት ለኛም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ስቶክሆልም ጉባዔ አስተባባሪ ኮሚቴ በጉጉት እና በደማቅ ዝግጅት ስንጠብቀው የነበረዉ ቀን ደርሶ እንዲህ በደማቅ እና ፍቅር በተሞላበት አገልግሎት አክብረነው አለፈ። እሁድ ሐምሌ 6 ጠዋት በደብሩ እና በእንግዶች ካህናትና ዲያቆናት በተአምረ ማርያም : በኪዳነ ጸሎት እንዲሁም በቅዳሴ ተጀመረ። ቅዳሴው እንዳበቃ ዕለቱን የሚያዘክር ያሬዳዊ መዝሙራት በህጻናት ጣፋጭ አንደበት ቀጥሎም በታላላቅ ወንድም እህቶቻቸዉ በሰንበት ተማሪዎች ቀረበ ። ሰዓቱ ወደ 10 ፡45 ገደማ ሲሆን በመምህር መጋቤ ሐዲስ ሚስጥረ ሥላሴ አባታችን አብርሃም በአምላክ ፊት ታዛዥ ታማኝና ትሁት ሆኖ በመገኘቱ ቅድስት ሥላሴ በጭንቀቱ ጊዜ በቤቱ ተገኝተው በበረከት እንደጎበኙት ፤ እንዲሁም የአንድነትና ሶስትነት ምስጢር እንደተገለጸለት ልብን በሚነካ ጥሩ አገላለጽ ካስተማሩን በኋላ እኛም መታመን የጎደለዉን ህይወታችንን ከአብርሃም በመማር እንዴት የአምላክን ጸጋና በረከት በህይወታች ን ማግኘት እንዳለብን ተረዳን። በዚህ ሰዓት በአስተባባሪ ኮሚቴ የምግብ እና መስተንግዶ ክፍል አባላት ሴቶች ማዕድ በማሰናዳት ሲሰማሩ በአንፃሩ ወንዶች በማስተናገድ ይተጉ ነበር ።

ከማዕድ መስተንግዶ በመቀጠልም ሰው ከሰው ጋር ሲኖር በፍቅር በመተሳሰብ በመከባበር እንዴት አብሮ መኖር እንደሚችል እንዲሁም በእምነት ስንኖር እንደ አብርሃም ለጋስ ልንሆን እደሚገባን የአብርሃምን አስራት ይዞ ወደ ካህኑ መልከ ጸዴቅ መሄድ በማስታወስ ነበር አባ ዘሚካኤል ትምህርታቸውን የጀመሩት። ቀጥለውም ምዕመኑም ትምህርቱን ተረድቶት ለመረዳት ከራሳቸው በመጀመር ለቤተክርስቲያን አስራት ማሰባሰብን ጀመሩ።

ለክፉ ቀን ደራሸ የሆነው ምዕመንም ትምህርቱ እንደ ገባው ሲያመለክት ለበረከት ይዞ የመጣው ሲሰጥ ያልያዘዉም ቃል በመግባት በጠቅላላዉ ወደ 80,000 ክሮኑር ተሰበሰበ ። የዲያቆናትና የካህናት አስተዋጽኦም ከፍ ያለ ነበር። ቀጥሎም ታቦተ ህጉ በዲያቆናትና በሰንበት ተማሪዎች ልዩ ዝማሬ በምእመናን እልልታና ጭብጨባ ታጅቦ ወደ ተዘጋጀለት ስፍራ ወጣ ። በመዘምራን በዓሉን የሚያዘክር ወረብ እና መዝሙር ከቀረበና አባ ዘሚካኤል ትምህርትና መልእክት በማስተላለፍ ካሳረጉ በኋላ የንግሱ ስነስርዓት ፍጻሜ ሆነ ።

 

እንዲህ እየደመቀ የተጋመሰዉ በአላችን አሁን ደግሞ ሰአቱ የመአድ መቁረስ ሆነና ምእመናን የተዘጋጀዉን የታፈጠ ምግብ እና መጠጥ በመስተንግዶ ክፍል አስተናባሪነት ተቋደሱ። በዚህ ግዜ የገቢ ክፍል አባላት በእለቱ የሚወጣ የእጣ ትኬት ይሸጡ ነበር ። በአባቶች የምስጋና ጸሎት የስጋን መብል አጠናቀን ወደ መንፈሳዊዉ ማእድ ተመለስን።

 

 ያብርሃምና ሳራ ጋብቻ ያርግላችሁ ፦ በሚል ርዕስ በዲያቆን ደረጀ የትዳር ሂወታችን  የነአብርሃምን ቢመስል እንዴት እንደሚባረክ ያብርሃምንና የሳራን ሂወት እያስቃኙ አስተማሩን ። በመዘምራን መዝሙር  ቀርቦ የእለቱ የመጨረሻ ትምህርት በመምህር መጋቢ ሃዲስ ሚስጥረ ሥላሴ ስለ መቻቻልና መተሳሰብ ፤ የሃሳብ ልዩነት እንኩዋን ቢኖር በመሃላችን በፍቅር በመወያየት መለያየት ወደኛ እንዳይመጣ እንዴት እድንተጋ የአብርሃም እና ሎጥን ታሪክ አስዳሰው አስተማሩን።

በደብሩ አስተዳዳሪ አባ መላከ ብርሃን ሃይለ ጊዬርጊስ የእለቱን ጉባየ በተመለከተ ጠቅለል ያለ መልእክት እና ለእንግዶች ምስጋና አቅርበው የአምላካችን ቃል ለህልዉናችን እንደሚያስፈልገን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ቃሉን መስማትና መተግበር እንደሚገባ አስገነዘቡን። የተሸጠውን ትኬት እጣ ካወጣንና ለእለቱ እድለኞች ከተሰጠ በኋላ በጸሎት እና በአባ ዘሚካኤል ዝማሬ የእለቱ መረሃ ግብር ፍጻሜ ሆኖዋል ። ምእመናንም የተዘጋጀዉን ሻይና ዳቦ እየቀመሱ በደስታ እያመሰገኑ ለቀጣዩ ጉባዬ በቸር ያድርሰን እያሉ በረከታቸዉን ይዘው ወደየቤታቸዉ ሄዱ ።

 

እንደ በደላችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ላስፈጸመን ክብርና ምስጋና አገልግሎት እና ውዳሴ ይሁን ለአብርሃሙ ሥላሴ !!!

 

 

ወስብሓት ለእግዚአብሄር፣

                                                                                                                                                                        ከመስተግዶ ኮሚቴ

የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም

ክርስቶስ ተን እሙታንበዓብይ ኋይል ወስልጣን

አሰሮ ለሰይጣን አግ ለዓዳም

ሰላም  –እም ይእዜሰ

ኮነ –ፍስሃ ወሰላም

«ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም፣ ወከመ ኀያል ወኅዳገ ወይን፣ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ = እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው ኀያል ሰውም፣ ጠላቱን በኋላው ገደለ፡፡»

 

 

 

የሚቀጥለው ሊንክ በመጫን ተጨማሪ ፎቶዎችን ይመልከቱ – የበዓለ ትንሳኤ አከባበር በመ/ጸ/ቅ/ሥ/ቤተክርስትያን ስቶክሆልም

 

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ

አዲስ የሰንበት ትቤት ስራ አስፈጻሚ አባላት ከደብሩ አስተዳዳሪበኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ መሰረት የሰንበት ት/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ።

በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቤተክርስትያኑ አስተዳደሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ፣ የአጥቢያው ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን ተገኝተዋል።

 

 

 

Read more

ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ

መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት በስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሌላቸው ሥልጣን አሽገው የምእመናንን የአምልኮ ነጻነት ለመገደብ በሞከሩ እና ችግሩ በሰላማዊ እና በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ ሀገረ ስብከቱ ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥረቶች ካለመቀበል አልፈው ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተላለፈው መመሪያ መሠረት ሀ/ስብከቱ ያዘጋጀውን የሠላም እና የእርቅ ጉባኤ ፋይዳ ቢስ በማደረግ በእምቢተኝነታቸው ጸንተው ይባስ ብለው አፍራሽ እንቅስቃሴ ባደረጉ እና እያደረጉ ባሉ የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አስተላለፈ።

Read more

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ምርጫ አካሄደ

pic-1ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ እና ሥራ አስኪያጁ መጋቤ አእላፍ ተወልደ ገብሩ እንዲሁም የአጥቢያው ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በተገኙበት የካቲት 02 ቀን 2006 ዓ.ም. በ S:t Jacobs Kyrka, Stockholm, Sweden ባደረገው አጠቃላይ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ ሕግና በሀገሩ የቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት:- መላከ ብርሃን አባ ገብረ ጊዮርጊስ ካሳዬ አለሙ፣ ዲ/ን ተሻለ ቢያዝን፣ ዲ/ን ኪሮስ አብርሃ፣ ታሪኩ ተመስገን፣ ይሁን ድሌ፣ በላይነሽ ገዝሄ፣ ጸደይ ሀጎስ፣ ታጠቅ ፍቃዱ እና ተስፋየ ገ/ማርያም የአጥቢያው ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ሆነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ መርጦ ሰይሟል።

የአዲሱ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ በጠቅላላ ጉባኤው በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት በደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ ካሳዬ አለሙ ሰብሳቢነት በቃለ አዋዲ ደንብ እየተመራ:-

Read more

ለየካቲት 23 2006 ዓ.ም. (March 2, 2014) በ Vårby skolan ይካሄዳል ተብሎ የተጠራውን ስብሰባ ሀ/ስብከቱ እውቅና የማይሰጠው መሆኑን ገለጸ

እንደሚታወቀው በምእመናን እና በቤተ ክርስቲያኑ የቀድሞ የሰበካ አስተዳደር መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትና በአስተዳደሩ በተወሰደው ቤተ ክርስቲያንን የማሸግ ኢ-ቀኖናዊ እርምጃ ላይ መፍትሄ ለመስጠት የሰ/ም/አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ከአንድም ሁለት ጊዜ ወደ ስቶክሆልም መምጣታቸው ይታወሳል። በእነዚህ ሁለት አበይት ስብሰባዎች የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ልዑካን እና ምእመናን በተገኙበት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ሃሳባቸውን እንዲያስረዱ በተደጋጋሚ በደብዳቤ፣ በስልክ፣ በኢሜል ቢጋበዙም ለመገኘት ፈቃደኛ አልሆኑም። ስለሆነም የምእመኑን መንፈሳዊ አገልግሎት የማግኘት መብትና የቤተ ክርስቲያኑን ደህንነት ለማስከበር ሲባል የካቲት 02 ቀን 2006 ዓ.ም. በ S:t Jacobs Kyrka, Stockholm , Sweden በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ኮሚቴ ተመርጧል። Read more