ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት

መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.

በዓቢይ ጾም ከሰርከ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፤ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፤ አክፍሎት፤ ቄጤማ ማሰር፤ ጥብጣብ፤ ጉልባን እና ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለ እነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈጻጸም መዛግብት አገላብጠን፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን አነጋግረን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

የ2007 ዓ.ም. የሆሳዕና በዓል

የ2007 ዓ.ም. የሆሳዕና በዓል አከባበር በፎቶ

{AG}images/eventgallery/Hosaena-2015{/AG}

{flike}{plusone}

ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ

ጥር 8 ቀን 2007 ..

በመልአከ ብርሃን አባ ገብረ ጊዮርጊስ 

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

 

Timketወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ” – ”ዳግመኛ ከውኃ እና ከመንፈስ ቅዱስ ወለደን”

”ወለደነ ዳግመ” ”ዳግመኛ ወለደን” ሲል የልደትን ሁለትነት ያሳያል። የመጀመሪያው ልደት የአዳም ጥንተ ተፈጥሮ ሲሆን፣ ሁለተኛው ልደት ከው ከመንፈስ ቅዱስ የተወለድነው ልደት ነው። ቀዳማዊ ልደታችን ወይም ተፈጥሮአችን ጥልቅ እንደሆነ ሁሉ፤ የሁለተኛው ልደታችንም የማይመረመር ምሥጢር በመሆኑ ምሥጢረ ጥምቀት ተብሏል። ለዚህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌሊት ወደ እርሱ ለመጣው ለአይሑድ መምህር ለኒቆዲሞስ ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳልና ድምጹን ትሰማለህ እንጂ ከየት እንደሚመጣ ወዴት እንደሚሔድም አታውቅም፤ ከመንፈስ ቅዱስ የሚወለድ ሁሉ እንዲሁ ነው። በማለት የዳግም ልደታችንን ረቂቅነት አስረድቶታል። (ዮሐ 3፥8) ልደት ቀዳማዊ ተአውቀ በደኃራዊ” – የመጀመሪያው ልደት በሁለተኛው ታወቀ” እንዲል።

ሁሉን ቻይ አምላክ አባታችን አዳምን በግብር አምላካዊ እንደ እርሱ ያለ ሳይኖር ካለመኖር ወደ መኖር በመልኩ፣ በአርዓያው፣ በምሳሌው አድርጐ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ማለትም ከው ከመሬት፣ ከነፋስና፣ ከእሳት  ፈጥሮ፤  የተፈጥሮአችን ተጠባቢ እርሱ ነውና፣ ለባዊት፣ ነባቢትሕያዊት ነፍስን ሰጥቶ (”ወነፍሓ ውስተ ገጹ ለአዳም መንፈሰ ሕይወት እንዲል) በቸርነቱ፣ በምሕረቱ ልደት ቀዳማዊን አድሎ፣ አካለ ሥጋን ከአካለ ነፍስ ጋር አዋሕዶ አክብሮ የፍጥረታት ሁሉ ገዥ አድርጐ በገነት አኖረው። (ዘፍ 2715)

Read more

ዮም ተወልደ ቤዛ ኩሉ ዓለም

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

ታህሳስ 28 ቀን 2007 ..

በመልአከ ብርሃን አባ ገብረ ጊዮርጊስ 

 

ወአመ በጽሐ ዕድሜሁ ፈነወ እግዚአብሔር ወልዶ ወተወልደ እምብእሲት።
ጊዜው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ።
 

Lidet

እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለመጠበቁና ከፈጣሪው ፈቃድ በመውጣቱ ላለፈው ሥርየት፣ ለሚመጣው ዕቅበት ይሆነው ዘንድ ከኃጢኣቱ ከውድቀቱ ለማዳን ለዓለም ቤዛ  አንድያ  ልጁን ላከ። ይኸውም:-

  – በሥጋ በደም ይዛመደን ዘንድ፤ (እብ 2፥14፣ ዮሐ 6፥56-57)
    ”ውእቱኒ ተሳተፎሙ በዝንቱ” እንዲል
  – ያጠፋናትን ልጅነት በልደት መንፈሳዊ (በጥምቀት)
    ዳግም ይወልደን ዘንድ፤ (ዮሐ 3፥5-6 ቲቶ 3፥4-5)
  – የጠላትንም ምክር ያፈርስ ዘንድ፤ (ቆላ 2፥14 ኤፌ 2፥15)
  – ከልጅ ልጅህ ተወልጀ አድንሃለሁ ያለውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ፤

በቤተልሔም ተወለደ፤ወኮነ ከመ ሰብእ” – ”ሰው ሆነ። (ፍልጵ 2፥7)

Read more

አእላፍ መላእክት

ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ 1፥14

በአባ ገ/ጊዮርጊስ ካሳዬ

ኅዳር 13 ቀን 2007 ዓ.ም. 

”በዛቲ ዕለት አዘዙነ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ከመ ንግበር ተዝካረ በዓሎሙ ለአእላፍ መላእክት” – ”በዚች ቀን የአእላፍ መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተክርስቲያን መምህራን አዘዙን” የኅዳር አሥራ ሦስት ስንክሳር። 

አባቶቻችን መምህራን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው በሠሩልን ሥርዓት መሠረት ኅዳር አሥራ ሦስት ቀን የእልፍ አእላፋት መላእክትን የመታሰቢያ በዓል ቤተ ክርስቲያን ታከብራለች። ስለዚህም በዚህ አጭር ጽሑፍ የቅዱሳን መላእክትን የስማቸውን ትርጓሜ፣ ተፈጥሯቸውንና ለተፈጠሩበት ዓላማ ያላቸውን አገልግሎትበብሉይ ኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳንና በሚመጣውም ዓለም የነበራቸውን፣ ያላቸውንና የሚኖራቸውን ድርሻ ባጭሩ እንመለከታለን።

Read more

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ – ሁለተኛ ሳምንት

+ + + እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ! + + +

ኑ! ቅዳሜ መስከረም 17 እና እሑድ መስከረም 18, በ Hallunda Folkets Hus ተገናኝተን ወንጌል እንማር! 

እግዚአብሔር አምላካችንን በዝማሬ እናመስግን። ዝርዝር መርሐ ግብሩን ከታች ይመልከቱ።

“የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” ራእይ 22፥17

Stockholm Silasse Gubae Meskerem 2007 Meskel

 

{flike}{plusone}

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

ማሳሰቢያ:- +++ የዕለተ ዓርብ የጉባኤ ቦታ ወደ St. Jacobs Kyrka ተቀይሯል

(Västra Trädgårdsgatan 2, T-bana: Kungsträdgården, ከኋላ ይውረዱ)

ሙሉ መረጃውን ከታች ይመልከቱ። እግዚአብሔር አምላክ ጉባኤያችንን ያቅናልን። +++

“የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” ራእይ 22፥17

Stockholm Silasse Gubae Meskerem 2007

{flike}{plusone}

አንግሰነው መጣን ቅዱስ ዑራኤልን

በጽዮን ጌታቸው

ነሐሴ 3 ቀን 2006 ዓ.ም.

አንግሰነው መጣን ቅዱስ ዑራኤልን
የተቦሪ ካሉት ወገኖች ጋር አብረን
መንፈስን የሚያድስ ጊዜን አሳልፈን
በደስታ በፍቅር በአንድነት ሆነን።
   ተሰባሰብንና አርብ ከሰአት
   እመሃል ከተማ ተቃጠርንበት።
በጸሎት ጀመርነው መንገዳችንን
አምላክ በቸርነት በሰላም አድርሶ እንዲመልሰን።
   ፍቅራችን ሲያስደስት እንዲሁ’ ዝማሬያችን
   ስናደርስ ምስጋና ለቸሩ አምላካችን።
በመሃሉም አረፍ አልንና ለምሳ
ከወደ አገልግሉ ምግብ ልናነሳ
ቀዩን ከአልጫው እንዲሁም ለስላሳ
ተበላ ተጠጣ ታጅቦ በጉርሻ።
   ተመልሰን ገባን ወደ መንገዳችን
   ለደካማዉ ስጋ ትንሽ ጉልበት ሰተን
   እኩለ ለሊት ላይ ደረስን ከደጁ
   ከሰላሙ መላክ ከቅዱስ ዑራኤል ከወደ አማላጁ።

Read more

በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ

በአባ ገ/ጊዮርጊስ ካሳዬ

ግንቦት 21 2006 ዓ.ም.

ዕርገት የሚለው ቃል መገኛው የግእዝ ቋንቋ ሲሆን፡-

መገኛ ቃሉም “ዐረገ” = “ከፍ አለ፣ ወጣ” የሚለው የግዕዝ ግሥ ይሆናል።

ዕርገት ማለት ደግሞ = ከፍ ማለት፣ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው።

በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ዕርገት ሁለት ዓይነት ነው፡-

የኅሊና ዕርገት እና

የአካል ዕርገት

Read more

የትንሣኤ 2 መዝሙርና ምንባባት

የትንሣኤ 2 መዝሙር (ከመጽሐፈ ዚቅ)

ትትፌሣሕ ሰማይ ወትታኃሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይጸውዑ አድባር ወአውግር ወኩሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ፡፡

ትርጉም: ሰማይ ይደሰታል ምድርም ትደሰታለች የምድር መሠረቶችም ቀንደ መለከትን ይንፉ /ይደሰቱ/ ተራሮችና ኮረብቶችም /ነገሥታት መኳንንት/ ይጩኹ/ይደሰቱ/ የምድረ በዳ እንጨቶችም ይጩኹ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን/ደስታን/ ታደርጋለች።

መልዕክታት

1ቆሮ. 15፥20-41
አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል፡፡ በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአልና፥ በሁለተኛው ሰው ትንሳኤ ሙታን ሆነ፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞት እንዲሁ በክርስቶስ ሁሉ ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ሰው ሁሉ በየሥርዐቱ ይነሣል፤ በመጀመሪያ ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ያመኑ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ይነሣሉ፡፡

Read more