ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም 7ኛ ሳምንት)

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡

ትርጉም:- ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምሕር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።

ምንባባት/መልዕክታት/

ሮሜ.7÷1-11 ወንድሞቻችን! ሕግን ለሚያስተውሉ እናገራለሁና÷ ሰው በሕይወት ባለበት ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚስትነት ታስራበት ከኖረችው ሕግ የተፈታች ናት፡፡

1ኛ ዮሐ.4÷18-ፍጻ በፍቅር መፈራራት የለም፤ ፍጽምት ፍቅር ፍርሀትን ወደ ውጭ ታወጣታለች እንጂ፤ ፍርሀት ቅጣት አለበት፤ የሚፈራም በፍቅር ፍጹም አይደለም፡፡  

የሐዋ.ሥራ.5÷34-ፍጻ በሸንጎዉም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የከበረ የኦሪት መምህር ስሙን ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ ተነሣ፤ ሐዋርያትንም ከጉባኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦

ምስባክ

መዝ.16÷ 3 “ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡

               አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡

               ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡” 

ትርጉም፦    በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤

               ልቤንም ፈተንኸው÷ ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡

               የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር÷ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ፡፡

ወንጌል

ዮሐ. 3÷1-11 ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ እንዲህ አለው፦

ቅዳሴ

ቅዳሴ ዘእግዝእትነ /ቅዳሴ ማርያም/

{flike}{plusone}