ቀዳሚት ሥዑር

 

ቀዳሚት ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አርፎ የዋለባት ዕለት በመኾኗ ‹ቀዳሚት ሥዑር› ወይም ‹ቀዳም ሥዑር› ትሰኛለች፡፡ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እኽል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

  

ሆሣዕና

በመ/ር ኃይለ ማርያም ላቀው

መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የኾነው ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደ ተቀመጠ ዅሉ ዛሬም ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት አድሮ የሕሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፡፡ እርሱ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅምና (መዝ. ፶፥፲፯፤ ኢሳ. ፷፮፥፪)፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜአችን ሳትጠልቅ በእምነት እግዚአብሔርን እንፈልገው፡፡ ሰላሙን ይሰጠን ዘንድም ንስሐ ገብተን ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› እያልን እናመስግነው፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት

መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.

በዓቢይ ጾም ከሰርከ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፤ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፤ አክፍሎት፤ ቄጤማ ማሰር፤ ጥብጣብ፤ ጉልባን እና ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለ እነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈጻጸም መዛግብት አገላብጠን፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን አነጋግረን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

 

 

የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ

አዲስ የሰንበት ትቤት ስራ አስፈጻሚ አባላት ከደብሩ አስተዳዳሪበኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ መሰረት የሰንበት ት/ቤት የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሄደ።

በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቤተክርስትያኑ አስተዳደሪ መልአከ ብርሃን አባ ገ/ጊዮርጊስ፣ የአጥቢያው ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን ተገኝተዋል።

 

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ...

ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልታዘዙ በቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አሳለፈ

መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት በስቶክሆልም መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የደብሩን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሌላቸው ሥልጣን አሽገው የምእመናንን የአምልኮ ነጻነት ለመገደብ በሞከሩ እና ችግሩ በሰላማዊ እና በመንፈሳዊ መንገድ እንዲፈታ ሀገረ ስብከቱ ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥረቶች ካለመቀበል አልፈው ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተላለፈው መመሪያ መሠረት ሀ/ስብከቱ ያዘጋጀውን የሠላም እና የእርቅ ጉባኤ ፋይዳ ቢስ በማደረግ በእምቢተኝነታቸው ጸንተው ይባስ ብለው አፍራሽ እንቅስቃሴ ባደረጉ እና እያደረጉ ባሉ የቀድሞው የሰበካ አስተዳደር አባላት እና ካህናት ላይ ሀ/ስብከቱ ቀኖናዊ ቅጣት አስተላለፈ።

ተጨማሪ ያንብቡ...

ማሳሰቢያ

ዘወትር እሁድ ጸሎተ ኪዳን፤ ስርዓተ ቅዳሴ እና ልዩ ስዩ መርሐግብሮች ስለሚኖረን በሰዓቱ ተገኝተን የበረከቱ ተሳታፊዎች እንድንሆን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን

ሰዓት፡ ከጠዋቱ 07፡00 - 12፡00

ቦታ፡
Bjorknåskyrkan
Vårmdovågen 622

ጥቆማ፡
ከ Slussen Buss 444, 422 ወይም 471 ይዘው Centeralplan ላይ ይውረዱ።

ግጻዌ

በፌስ ቡክ ያግኙን